ክሪስታቮ ደጋማ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ክሪስታቮ ደጋማ (ከ፲፭፻፰ አካባቢ እስከ ነሐሴ ፳፮ ቀን ፲፭፻፴፬ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ የፖርቹጋሎችን ጦር መሪ የነበረ (1541-43) ሲሆን የግራኝ አህመድን ሰራዊት ቁጥሩ በጣም ባነሰ ሰራዊት አራት ጊዜ አሸንፎች በአምስተኛው ጊዜ ተማርኮ ሃይማኖቴን አልቀይርም ሲል የተገደለ አዋጊ ነበር። ሪቻርድ በርተን የተባለ የታሪክ ተመራማሪ ክሪስታቮን በጀግኖች ዘመን የተወለደ ቀደምት ጀግና ነበር ሲል አድንቆታል።[1] በሌላ በኩል ክሪስትቮ የታዋቂው አለም አቀፍ ተጓዥ ቫስኮ ደጋማ ልጅ ነበር።