ግራኝ አህመድ
ኢማም አሕመድ / From Wikipedia, the free encyclopedia
በተለምዶው ግራኝ አሕመድ ተብሎ የሚታወቀው የጦር መሪ ሙሉ ስሙ ኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ሲኾን የኖረውም ከ1507 እስክ ታህሳስ 21፣ 1543 (እ.ኤ.አ) ነበር። [1]) በዘመኑ በእስልምና ሃይማኖት የኢማምነት ደረጃ የደረሰ ሲኾን የአዳል ግዛት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የጥንቱን የኢትዮጵያ ክፍል በመምራት እንዲሁም በዘመኑ የነበሩትን ነገሥታት ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንዲያፈገፍጉ በማድረግ በታሪክ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ 3/4ኛ የሚኾነውን የኢትዮጵያ ክፍል ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችሏል። አንድ አንድ የታሪክ ተመራማሪዎችም የግራኝ አሕመድ ሰራዊት ከሞላ ጎደል በሱማሌ ጎሳ ሰዎች የተድሎችን በመቀዳጀቱ ምክኒያት በዚህ ስያሜ እንደጠሩት ይነገራል። ይህ መሪ ከ1529 እስከ 1543 ከነበሩት የመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነገስታት ጋር ጦርነት እንዳረገ ታሪክ ይዘግባል።[1]