1967
From Wikipedia, the free encyclopedia
1967 አመተ ምኅረት
- መስከረም 2 ቀን - ኰሙኒስት ደርግ የኢትዮጵያን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አሠሩዋቸው።
- መስከረም 5 ቀን - ጄኔራል አማን አንዶም የደርግ ሊቀ መንበር ተሰየመ።
- ኅዳር 14 ቀን - አማን አንዶምና ሌሎች ባለሥልጣናት በደርግ ተገደሉ፤ ተፈሪ በንቲ በኅዳር 19 ቀን ሊቀ መንበር ተሾመ።
- ኅዳር 15 ቀን - የ«ድንቅ ነሽ» አጽም በአፋር ክልል ውስጥ ተገኘ።
- ታኅሣሥ 4 ቀን - ማልታ ንግሥት ኤልሳቤጥን በይፋ ትቶ ሪፐብሊክ ሆነ።
- ታኅሣሥ 23 ቀን - የማላዊ ዋና ከተማ ከዞምባ ወደ ሊሎንጔ ተዛወረ።
- ሚያዝያ 9 ቀን - የፕኖም ፔን ውድቀት፣ የክመር ሩዥ ኰሙኒስት ሃያላት መላውን ካምቦዲያ ያዙ።
- ሚያዝያ 22 ቀን - የሳይጎን ውድቀት፣ የስሜን ቬትናም ኰሙኒስት ሃያላት መላውን ደቡብ ይዘው የቬትናም ጦርነት ተጨረሰ።
- ግንቦት 8 ቀን - የሲኪም መንግሥት ወደ ሕንድ ተጨምሮ ሲኪም ክፍላገር ሆነ።
- ሰኔ 18 ቀን - ሞዛምቢክ ከፖርቱጋል ነጻ ወጣ።
- ሰኔ 28 ቀን - ኬፕ ቨርድ ከፖርቱጋል ነጻነቱን አገኘ።
- ሰኔ 29 ቀን - ኮሞሮስ ነጻነት ከፈረንሳይ አዋጀ።
- ሐምሌ 5 ቀን - ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ነጻነት ከፖርቱጋል አገኘ።
- ነሐሴ 15 ቀን - የኩባ ሃያላት ደቡብ አፍሪካን ለማቃወም ወደ አንጎላ ጦርነት ገቡ።
- ነሐሴ 17 ቀን - የቭየንትዬን ውድቀት፣ የፓጤት ላው ኰሙኒስት ሃያላት መላውን ላዎስ ያዙ።