አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ዋና ከተማ / From Wikipedia, the free encyclopedia
አዲስ አበባ (Addis Abeba) ወይም በረራ ፣አዱ ገነት ወይም በተለምዶ "ሸገር" የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት ። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት የፌደራል ከተማነትን ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በ1999 አ.ም በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ወደ 2,739,551 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ ትልቋ ከተማ ናት።[1]
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ተጨማሪ ፡ ዋቢ ፡ ያስፈልገዋል ። እባክዎን ፡ ተገቢ ፡ ምንጮን ፡ በመጥቀስ ፡ ያሻሽሉት ። መረጋገጥ ፡ የማይችሉ ፡ ዋቢዎች ፡ ጥያቄ ፡ ሊነሳባቸው ፡ ወይም ፡ ሊወገዱ ፡ ይችላሉ ። (፯ ነሐሴ ፳፻፮) |
Quick Facts
አዲስ ፡ አበባ | |
የአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀሰ ህንፃዎች 2023 | |
አገር | ኢትዮጵያ |
የተቆረቆረችው | ፲፰፻፸፰ |
ከንቲባ | አዳነች አቤቤ (ምክትል) |
የቦታ ስፋት | |
• አጠቃላይ | 527 |
ከፍታ | 2,355 ሜ. |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 3,384,569 |
ድረ ገጽ | addisababacity.gov.et |
Close
ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍልውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን ወደ አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል።
ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ነች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።