አንጎላ
From Wikipedia, the free encyclopedia
አንጎላ፣ በይፋ የአንጎላ ሪፑብሊክ (ፖርቱጊዝ: República de Angola ፣ ኪኮንጎ: Repubilika ya Ngola) በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች መሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቱጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።
የአንጎላ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: ወደፊት አንጎላ! (ፖርቱጊዝ) Angola Avante! |
||||||
አንጎላ በሰማያዊ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ሏንዳ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፖርቱጊዝ | |||||
መንግሥት ፕሬዝዳንት |
ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ João Lourenço |
|||||
ዋና ቀናት ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፷፰ (ኖቬምበር 11, 1975 እ.ኤ.ኣ.) |
João Lourenço የመሬት_ስፋት = 1,246,700 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2014 እ.ኤ.አ. ግምት የ ቆጠራ |
25,789,024 (50ኛ) 5,646,177 |
|||||
ገንዘብ | ክዋንዛ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
የስልክ መግቢያ | +244 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .ao |