አምባሰል
From Wikipedia, the free encyclopedia
አምባሰል በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኝ ወረዳ ሲሆን፤ ስሙ በዚህ ወረዳ ውስጥ ከሚገኝ አምባ ስም ይመነጫል። አምባሰል ወረዳ፣ በደቡብ ምዕራብ የባሽሎ ወንዝ ከተንታ ወረዳ ሲለየው፣ በደቡብ የባሽሎ ገባሪ የሆነው ወላኖ ወንዝ ከኩታበር፣ እንዲሁ የ ሚሌ ወንዝ ደግሞ በስተ ደቡብ ምስራቅ ከተሁለደሬ ወረዳ ይለየዋል። 44% የሚሆነው የወረዳው ክፍል ተራራማ፣ 36% ወጣ ገባ፣ 12% ገደላማ ሲሆን 7.5% ብቻ ለጥ ያለ ሜዳ ነው። ስለሆነም በዚህ ወረዳ አራት አይነት የአየር ንብረቶች ይገኛሉ፦ ውርጭ፣ ደጋ፣ ወይና ደጋ እና ቆላ፣ እያንዳንዳቸው .47%፣ 29.53%፣ 49.64%፣ 20.36% ይይዛሉ። የዚህ ወረዳ ታላቁ ከተማ ውጫሌ ሲሆን በአካባቢው በሚገኝ የተፈጥሮ ከሰል ክምችት ይታወቃል። የኢጣሊያ ወራሪ ሃይል ይህን የከሰል ክምችት አገር እስከለቀቀበት ዘመን ድረስ ይጠቀም ነበር[1]።