መለስ ዜናዊ
From Wikipedia, the free encyclopedia
መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስ) (ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ነበሩ። በአድዋ ትግራይ የተወለዱ ሲሆን ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም አንስተው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህአዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ቆይተዋል።
Quick Facts መለስ ዜናዊ, ፕሬዝዳንት ...
መለስ ዜናዊ | |
---|---|
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር | |
ከነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. | |
ፕሬዝዳንት | ነጋሶ ጊዳዳ መ/አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ |
ቀዳሚ | ታምራት ላይኔ (ተግባራዊ) |
ተከታይ | ኃይለማሪያም ደሳለኝ |
የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት | |
ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. | |
ጠቅላይ ሚኒስትር | ተስፋዬ ዲንካ ታምራት ላይኔ |
ቀዳሚ | ተስፋዬ ገብረ ኪዳን (ተግባራዊ) |
ተከታይ | ነጋሶ ጊዳዳ |
ሌላ ስም | ለገሠ ዜናዊ አስረስ (የትውልድ) |
የተወለዱት | ግንቦት 1 ቀን 1947 ዓ.ም. አድዋ፣ ኢትዮጵያ |
የሞቱት | ነሐሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ብረስልስ፣ ቤልጅግ |
የፖለቲካ ፓርቲ | ሕወሐት፣ ኢህአዴግ |
ባለቤት | አዜብ መስፍን |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና |
Close
አቶ መለስ ዜናዊ አባታቸው (አቶ ዜናዊ አስረስ ከጎዣም አገው ቤተሰባዊ ትስስር እንዳላቸው ይታመናል[1]) የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፣ በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው።
መለስ በታወቀው ጀነራል ዊንጌት 2ኛ ደረጃ ተምህርት ቤት የተማሩና ከአጼ አህለስላሴ የኮከብ ተማሪዎች ሽልማት የተሸለሙ፣ ከዛም ወደ በረሃ ወርደው በታጋይነት ከመሰለፍቸው በፊት፤ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሜዲካል ፋክልቲ ተማሪ ነበሩ። ትግርኛ፣አማርኛና፡ እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ።
መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ባደረጓቸው አስተዋፅኦዎች የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው ይባላሉ፡፡ ኢትዮጵያም እንደ እርሳቸው ያለ መሪ አግኝታ እንደማታውቅ በሰፊው ይነገራል፡፡