F
From Wikipedia, the free encyclopedia
F / f በላቲን አልፋቤት ስድስተኛው ፊደል ነው።
More information ግብፅኛ ሐጅ, ቅድመ ሴማዊ ዋው ...
Close
More information የላቲን አልፋቤት, ተጨማሪ ምልክቶች፦ ...
Close
የ«F» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኢው» (Υ, υ) ለማመልከት ተጠቀመ። ቅርጹ ትንሽ ተለውጦ ግን ተነባቢውን «ው» ለማመልከት Ϝ ϝ («ዋው» ወይም «ዲጋማ») ተጠቀመ። ከዚህ በኋላ «ው» የሚለው ተነባቢ ከግሪክኛ አነጋገር ስለ ጠፋ፣ «Ϝ ϝ» ለቁጥር (፮) ብቻ ሆነ። (ደግሞ ስቲግማ ይዩ።)
በኤትሩስክኛ ደግሞ «F» ለተነባቢው «ው» ይወክል ነበር። የ«ፍ» ድምጽ ለመወክል «FH» ተጻፈ። በሮማይስጥ ሌላ ምልክት «V» ለ«ው» ስለ ተጠቀመ፣ በላቲን ፊደል ፊደሉ «F» ለ«ፍ» ሊወክል ጀመር።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ወ» («ዋዌ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዋው» ስለ መጣ፣ የላቲን 'F' ዘመድ ሊባል ይችላል። እንዲሁም የላቲን U፣ V፣ W፣ እና Y ሁሉ ከ«ዋው» ደረሱ።