የመን (አገር)
From Wikipedia, the free encyclopedia
የየመን ሪፐብሊክ በዓረቢያ ምድር ወይንም ፔኒሱላ በደቡብ ምዕራብ እስያ የምትገኝ ሀገር ስትሆን 530,000 ስኩኤር (ካሬ) ኪሎ ሜትር ስፋት እና ከ23 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ነዋሪ አላት። ዋና ከተማዋ ሰንዓ በመባል ይጠራል። ጥንታዊቷ የመን የሳብያን መናገሻ ስትሆን ግዛቱም እስከ አሁኗ ኢትዮጵያ የሚደርስ ነበር። ብዙም ሳይቆይ በአይሁዱ ግዛት ሂሚያራት ቁጥጥር ስር ዋለች። በስድስት መቶኛ ክፍለ ዘመን እስልምና በየመን ውስጥ በአጭሩ ተንሰራፋ። የመን ከአስር ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ ሁለተኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ ክልሎቿ በእንግሊዝ እና በኦቶማን ቱርኮች ተከፍላ ትመራ ነበር። ፕሬዝዳንት ሳላህ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የመን በአመፅና ተቃውሞ ታጅባለች። ይህም በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የእድገት ቀውስ አስከትሎባታል።
Quick Facts የመን ሪፐብሊክ الجمهورية اليمنية ...
የመን ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: الجمهورية المتحدة |
||||||
ዋና ከተማ | ሳና ዓደን |
|||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ዓረብኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
የሽግግር ዓብድራብቡህ ማንሱር ሓዲ ዓህመድ ዖበኢድ ቢን ዻግህር |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
503,891 (49ኛ) <1 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2013 እ.ኤ.አ. ግምት |
25,408,000 (160ኛ) |
|||||
ገንዘብ | የመን ሪኣል | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +3 | |||||
የስልክ መግቢያ | 967 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .ye اليمن. |
Close
- (ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ!)