ፍልስፍና
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ «Philos» /ፊሎስ/ ማለትም ፍቅር እና፣ «sophos» /ሶፎስ/ (ጥበብ) የተገኘ ውሁድ ነው። በቀጥታው የጥበብ ፍቅር ወይም ፍቅረ ጥበብ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በመሆኑም ፍልስፍና እውቀትን፣ እውነትን፣ ጥበብን መውደድ፣ መሻት፣ መመርመር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ባንድ በኩል ወደ ጥበብ የተሳበ፣ ጥበብን የወደደ እንደዚሁም የጥበብ ባለሟልን የሚያመለክት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጥበብን ወዶ ሌላውም እንዲወድ ምክንያት የሚሆን ለማለት ይውላል። ይህ የጥናት ክፍል በዋናነት ነገሮችን በመላምታዊ መንገድ ለመመርመር ይሞክራል።
የፍልስፍናን ምንነት ለማወቅ የሚጠይቃቸውን ዋነኛ ጥያቄዎች እንመልከት።