ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
From Wikipedia, the free encyclopedia
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች (የድሮ ክልሎች 7,8,9,10,11) በኢትዮጵያ ከሚገኙ አስራአንድ ክልሎች አንዱ ነው። 105,887.18 ካሬ ኪ.ሜ. ቦታ የሚሸፍን ሲሆን[1] በምዕራብ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ ሰሜን ምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ከኬንያ ጋር ይዋሰናል።[2] የክልሉ ዋና ከተማ ሃዋሳ ሲሆን ሌሎች ትልቅ ከተማዎች ወልቂጤ፣ ጉብርየ፣ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና፣ቡታጂራ፣ ክብረመንግሥት፣ ያቤሎ፣ አላባ፣ አገረሠላም፣ አለታዎንዶ፣ ቦዲቲ፣ ወንዶ፣ ዲላ፣ ይርጋለም፣ ጂንካ፣ ሶዶ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን ተፈሪ ናቸው።
Quick Facts
ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል | |
ክልል | |
የደቡብ ክልልን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ርዕሰ ከተማ | አዋሳ |
የቦታ ስፋት | |
• አጠቃላይ | 105,887.18[1] |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 17,359,008[1] |
ድረ ገጽ | http://www.snnprs.gov.et/ |
Close
ክልሉ በ፲፫ ዞኖችና ፰ ልዩ ወረዳዎች በ፳፪ የከተማ አስተዳደሮች የተደራጀ ሲሆን በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ መሠረት 15,042,531 ሕዝብ የሚገኝበት ሲሆን ይህም ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 20.4% ይሸፍናል።[2] ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ፶፮ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚኖሩ ሲሆን የእነዚህም ቋንቋዎች በአፍሮ እስያዊ (ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ ንዑስ ክፍሎችን ጨምሮ) እና ናይሎ ሳህራዊ የቋንቋ ቤተሰቦች ይመደባሉ።[2]