የዓለም ዋንጫ
በከፍተኛ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን የተካሄደ የአለም አቀፍ ማህበር የእግር ኳስ ውድድር / From Wikipedia, the free encyclopedia
የዓለም ዋንጫ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር አባል አገሮች የወንድ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚከናወን ውድድር ነው። ከ፲፱፻፳፪ ዓ/ም ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይካሄዳል። ነገር ግን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት የ፲፱፻፴፬ ዓ/ም እና የ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ውድድሮች ሲሰረዙ እስካሁን አሥራ ዘጠኝ ውድድሮች ተካሂደዋል። የዋንጫና ደረጃ ጨዋታዎቹ በዓለም በብዙ ተመልካቾች ከሚታዩ የስፖርት ዝግጅቶች አንደኛ ነው። በደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የ ፳፻፪ቱ ፲፱ ኛው የዋንጫ ውድድር በ ፩ ነጥብ ፩ ቢሊዮን ሰዎች እንደታየ ይገመታል።