እንቁራሪት
From Wikipedia, the free encyclopedia
እንቁራሪት የአምፊቢያን አይነት ስትሆን መልኳ እንደ ሌላ ጓጉንቸር ነው። ሆኖም፣ ከሌላ ጓጉንቸር በተለየ መልኩ፣ ከውሃ ዳር ይልቅ በደረቅ ቦታ መኖርን ታዘወትራለች፣ ቆዳዋም እየቆረበጠ የሚሻክር ነው። የኋላ እግሮቿ አጭር ስለሆኑ፣ ከመዝለል ይልቅ መራመድን ታዘወትራለች። ከጓጉንቸር ክፍለመደብ ብዙ አስተኔዎች «እንቊራሪት» ተብለዋል። ጉርጥ አንዱ የእንቁራሪት አስተኔ ሲሆን የብዙ ጉርጦች ቀለም ወደ ቡኒ የተጠጋ ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
More information ?እንቁራሪት, ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ ...
Close
እንቁራሪት በውሃ ና በየብስ ትኖራለች። ወደ በየብስ ስትወጣ በሳምባዋ ትተነፍሳለች። በውሃ ውስጥ ደግሞ በስንጥብ(ጊል)ነው።