ኒል አርምስትሮንግ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኒል አርምስትሮንግ አሜሪካዊ የህዋ መንኩራኩር አብራሪ ሲሆን በጁላይ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. በአፖሎ ፲፩ የመንኩራኩር ጉዞ ጨረቃ ላይ በመራመድ የመጀመሪያ የሰው ልጅ ነው። ይህ በጣም ጎበዝ ሥራ ነው። ናሳን እ.ኤ.አ በ1962 ከመቀላቀሉ በፊት የአሜሪካ ባህር ሃይል ውስጥ የተዋጊ ጀት አብራሪ ሆኖ በኮሪያ ጦርነት ወቅት ተሳትፎ ነበር። ናሳን ተቀላቅሎ ከአራት አመት በኋላ ወደ ህዋ የመጀመሪያውን ጉዞ ያደረገ ሲሆን በዛም ጉዞ የመጀመሪያውን በሰው ልጅ የታገዘ የመንኩራኩሮች መያያዝ አከናውኗል። ከዚህ ጉዞው በኋላ ወደ ህዋ ያልሄደው ኒል በተወለደ በ 82 አመቱ በኦገስት 26፣ 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። [1]