ጋኔን
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጋኔን (ነጠላ) ወይንም አጋንንት (ብዙ ቁጥር) የእርኩስ መንፈስ አይነት ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተመዘው በተስፋፉ ጽሑፎች ላይ የዚህ መንፈስ ታሪክ/አፈ-ታሪክ ተጽፎ ይገኛል። ለምሳሌ ቀኖናዊ ባልሆኑት ስነ ፍጥረት እና ሰይፈ ስላሴ በተባሉ የግዕዝ መጻሕፍት።
አሁንም ብዙው ህብረተሰብ እንዲህ ያስባል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሚጠቀሱ፣ እስካሁን ድረስ በዓለም ዙሪያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ትምህርት እንዲህ ይመስላል። አጋንንት የሳይንስ እውቀት ባላቸውም ሆነ በሌላቸው ኢትዮጵያውን ዘንድ እጅግ ከፍተኛ ፍርሃቻን የሚፈጥር አስተሳሰብ ነው። ነገር ግን የአጋንንት ታሪክ የሚመነጨው የሳይንስ አስተሳሰብ ባልተስፋፋበትና ስለቫይረስም ሆነ ጀርም በማይታወቅበት ዘመን ሲሆን ዘመናዊው የሳይንስ አስተሳሰብ ከዚህ ይለያል፣ እንደሚከተለው ይላል፦ ዋና ዓላማውም የበሽታዎችን አመጣጥ በሚያሳምን መልኩ ለመረዳት እና ለመተንበይ ነበር። ይሄ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ያልተማረ ህብረተሰብ የሚሰራበት የነበር ነው። ስለሆነም ሆድ ቁርጠት፣ ጉስምት፣ ብድብድ ወዘተ በአጋንንት ምክንያት የሚመጡ ተደርገው ይታሰቡ ነበር።