ጋምቤላ (ከተማ)
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጋምቤላ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ናት። በላቲቱድና በሎንጂቱድ 8°15′ ሰሜን ኬክሮስ እና 34°35′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ትገኛለች።
በ1998 የማዕከላዊ የስታትስቲክ ትመና መሰረት የ31,282 ሰዎች መኖሪያ ስትሆን ከነሱም መሃከል 16,163 ወንዶችና 15,119 ሴቶች ይገኙባታል። ጋምቤላ የአኙአክ እና የኑር ጎሳዎች መኖሪያ ስትሆን የየራሳቸው ገበያ በጋምቤላ ውስጥ አላችው። ከተማዋ የአንድ ኤርፖርት ባለቤትና የጋምቤላ ብሄራዊ ፓርክ ተጓዳኝ ናት።