ደምበጫ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ደምበጫ በጎጃም ክፍለ ሃገር የምትገኝ ከተማ ስትሆን ከአዲስ አበባ 340 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች። አረቂ ማር ና ቅቤ በማምረት የታወቀች ከተማ ናት። በአካባቢው በሚገኘው ፍል ውሃም እንዲሁ በአጠቃላይ ጎጃም ትታዎቅ ነበር።
ደምበጫ በታሪክ ማህደር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፍራ የምናገኛት ቀዳማዊ ዮሐንስ ከይባባ ወደ ጎንደር ግንቦት 1፣ 1675 ዓ.ም በአካባቢው እንዳለፈ በዜና መዋዕሉ ላይ ስለተመዘገበ ነው[2][3] ።