የወባ ትንኝ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የወባ ትንኝ ወይንም ቢንቢ የዝንብ አይነት እንስሳ ናት። የትንኝ ሴቶች ተዋህስያን ስለሆኑ በደመ ሙቅ እንስሳት ላይ አርፈው፣ የእንስሳውን ቆዳ በሹል አፋቸው ከበሱ በኋላ፣ ምራቃቸውን ይረጩበታል። ይህን እሚያደርጉት የበሱት እንስሳ ደም እንዳይረጋ ነው። በእዚህ ሁኔታ ነገሮችን ካመቻቹ በኋላ፣ የአረፉበትን እንስሳ ደም ይመገባሉ ማለት ነው።
More information ?የወባ ትንኝ, ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ ...
?የወባ ትንኝ | ||||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
የቢጫ ወባ ቢንቢ ሰውን ስትነክስ | ||||||||||||||||
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||||
| ||||||||||||||||
Close
በሽታ የሚያጋቡት፣ ቆዳ ሲበሱ ወይንም ደም ሲመጡ ሳይሆን፣ ምራቃቸውን ሲረጩ ነው። ለእዚህ ምክንያቱ በምራቃቸው ውስጥ አደገኛ ተውሳኮች ጎጆአቸውን ቀልሰው ስለሚኖሩ ነው[1][2] ። በመገቡበት ቦታ ላይ እከክ የተነሣበት ምክንያት ምራቃቸው ቆዳውን ስለሚያሳውከው ነው።
ወንዶች ትንኞች የአበባ ጣዝማ ነው ምግባቸው። ሴቶቹም እንዲሁ የአበባ ጣዝማ ይመገባሉ፣ ሆኖም እንቁላል ሊጥሉ ሲሉ ብዙ ፕሮቲን ስለሚያስፈልጋቸው፣ የግዴታ ደም መምጠጥ አለባቸው። አለበለዚያ እንቁላል መጣል አይችሉም።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |