የኮርያ ጦርነት
From Wikipedia, the free encyclopedia
የኮርያ ጦርነት በኮርያ ከሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር።
ይህ መጣጥፍ የውክፔዲያ የአቀማመጥ ልምዶችን እንዲከተል መስተካከል ይፈልጋል። |
የኮርያ ጦርነት | |||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|
የቀዝቃዛው ጦርነት ክፍል | |||||||
| |||||||
ወገኖች | |||||||
የተባበሩት መንግሥታት (ውሳኔ ፹፬) ደቡብ ኮሪያ |
ሰሜን ኮሪያና አጋሮች፦ የኮሪያ ዴሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ | ||||||
የደረሰው ጉዳት | |||||||
የሞቱ፦ የቆሰሉ፦ የጠፉ፦ ጠቅላላ፦ |
የሞቱ፦ የቆሰሉ፦ የጠፉ፦ ጠቅላላ፦ |
የኮሪያ ዘማቾች ትውስታ
ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም” “አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም”
በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት 350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡
ለኮሪያ ዘመቻ እንዴት ነው የተመረጡት?
በመሠረቱ የገበሬ ልጅ ነኝ፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ ተብዬ አይደለም ወደ ወታደራዊ ዘመቻ የገባሁት፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት በሕፃንነቴ ከአባቴ ጋር ጫካ ለጫካ ተንከራትቻለሁ፡፡ በ1939 ዓ.ም ወታደርነት ተቀጠርኩ፡፡ የተወለድኩት በ1922 ዓ.ም ነው፡፡ ወታደር በሆንኩ በአምስት ወይ በስድስት ዓመት ኮርያ ዘመትኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር ስዘምት ማንበብና መፃፍ አልችልም ነበር፡፡
አሁንም ድረስ?
አይደለም፡፡ እዚያው ኮርያ እያለሁ ዘመድ ደብዳቤ ፃፈልኝ፡፡ ሃምሳ አለቃ ንጉሤ ወልደሚካኤል የሚባል ጓደኛዬን ፃፍልኝ ስለው ሂድ አልጽፍም አለኝ፡፡ ንዴት ያዘኝና ወንጌሌ ቆስጣ ለሚባሉ አለቃዬ ጋዜጣ ስጡኝና ፊደል ልማርበት አልኳቸው፡፡ ፊደል ጭምር ሰጡኝ፡፡ በዚያው በጓደኞቼ አጋዥነት ተለማምጄ ስሜን መፃፍ ቻልኩ፡፡ በሦስት ወር ደብዳቤ ለቤተሰብ ጽፌ ደብዳቤዬ እንደደረሳቸው ቤተሰቦቼ ሌላ ደብዳቤ ላኩልኝ፡፡ ጥሩ አለቆች ስለነበሩኝም እዚህ ስመለስ ጫካ ወስደው ጥቁር ሰሌዳ በማሸከም ያስተምሩን ነበር፡፡ የማታ ትምህርትም ገብቼ ነበር፡፡ ዘመቻውን ከሦስተኛው ቃኘው ጋር በኮሎኔል ወልደዮሐንስ ሽታ አዝማችነት ነበር የዘመትኩት፡፡
እዚያ ሲደርሱ ከነበረው ምን ያስታውሳሉ?
የመጀመሪያውን ቅኝት ስንወጣ በእኔ መቶ አዛዥነት ነበር፡፡ የመጀመርያው ተኩስ ሞትና መቁሰልም የደረሰው በእኛ ላይ ነው፡፡ የዘመትነው በግንቦት ወር 1945 ዓ.ም ነበር፡፡ የመጀመሪያው ቃኘው የዘመተው በ1943 ዓ.ም ነበር፡፡ አንድ ሞቶብን ሁለት ቆሰሉ፡፡ አንደኛው ቁስለኛ እጁ ተቆረጠ፡፡ የሞተውንና ቁስለኞቹን ይዘን ወደ ወገን ጦር ተቀላቀልን፡፡
ሁለተኛው የጦር ግንባር ከፍተኛው የቲቮ ተራራ ነው፡፡ እዚያ ላይ በመከላከል ላይ ነበርን፡፡ ጓደኛዬ እዚህ ውስጥ አለ (በጦርነቱ የተሰውትን ሃውልት እያሳዩ) በዳኔ ነገዎ ይባላል፡፡ መከላከያ ውስጥ አንድ ላይ ነበርን፡፡ ባንከር አለ፡፡ ድንገት ቢተኮስ እዚያ እንግባ ስለው እምቢ አለ፡፡ እየጐተትኩት እያለሁ ጥይት ተተኮሰ፡፡ እሱን በጣጥሶ ሲጥል እኔን አፈር ከአንገት በታች ቀበረኝ፡፡ ጥይቱ እያበራ ሲመጣ እኔ ዘልዬ ስወድቅ እሱን በጣጠሰው፡፡ ከ45 ደቂቃ ቁፋሮ በኋላ ነው ያወጡኝ፡፡ ከዚያ የጓደኛዬን ሰውነት በዳበሳ ፈልገን በራሱ ሸራ አድርገን ለመቃብር አበቃነው፡፡ ጦርነቱ ባይቆም ያ ሁሉ ሠራዊት ያልቅ ነበር፡፡
ግን አንድም አልተማረከም?
አንድም አልተማረከም፡፡ ዘማቹ ይፋቀራል፡፡ ይከባበራል፡፡ ጓደኛህ ቢሞት እንኳ ሬሳውን ጥለህ አትሄድም፡፡ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም፡፡ አመት ከሰባት ወር እዚያ ቆይቻለሁ፡፡ ጦርነቱም የቆመው እዚያ እያለን ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በየቀጠናው ጥበቃ እናደርግ ነበር፡፡
አሁን በእርቁ ለሰሜን ኮርያ ተሰጠ እንጂ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሰሜን ዘልቀናል፡፡ ብዙ ምሽግ መቆፈራችን ነው አንድም እዚያ ብዙ ያቆየን፡፡ ሀገሩም የራሱን ጦር እስኪያደራጅ መቆየቱ የግድ ነበር፡፡ ነሐሴ 29/1946 ዓ.ም ተመልሰን አዲስ አበባ ገባን፡፡ ሌሎቹ የተማረኩት ምን አልባት በምቾት ብቻ መኖር ስለለመዱ ይመስለኛል፡፡ እኔ ከወገኔ ተለይቼ እጄን የምሰጥበት ምክንያት የለም፡፡ ሄጄ ማን እጅ ነው የምገባው? ጠላት እጅ፡፡ ስም ያለው ሞት መሞት እንጂ ሁለት ሞት አልሞትም፡፡
የመጀመሪያው ቃኘው ሻለቃ ሲሄድ እርስዎ የት ነበሩ?
ሠራዊት ውስጥ ነበርኩ፤ ሐረር የልዑል መኮንን ቤተመንግስት ጥበቃ ላይ ነበርን፡፡ በ1944 ወደ አዲስ አበባ ተዛውረን መጣን፡፡ ከዚያ ተመልምዬ ነው ወደ ኮርያ ለመሄድ የበቃሁት፡፡ እንዴት እንደተመለመልን አላውቅም፡፡ ይኼን የሚያውቁት መልማዮቹ ናቸው፡፡ የታዘዘውን ፈፃሚ ጠንካራ ሞራል ያለው ሠራዊት ተመርጧል፡፡
ከማን ጋር የምትዋጉት? የውጊያ ብቃታቸውስ ምን ይመስላል?
እነዚያ ሰሜን ኮርያ፣ ሶቭየት ሕብረት፣ ቻይናና ተባባሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ብርቱ ስልት አላቸው፡፡ በጨበጣ ውጊያ የወደቀልህ መስሎ መትቶ ይጥልሃል፡፡ የእኛዎቹ በተለይ አሜሪካኖች እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ታንክ፣ መድፍ… ታንክ ላይ የሚጠመደው ጀነራል መድፋቸውማ የተለየ ነው፡፡ ይኼ መድፍ በጣም በርቀት መምታት የሚችል ነው፡፡ እዚህ ሲተኮስ እዚያ ፈንድቶ ርቀቱን ይጨምራል፡፡ አውሮፕላኖችም አሉት - የኛ ወገን፡፡ አንድ ጦር ከተከበበ በአየር ይመታል አካባቢው፡፡ በዚህ መልኩ 70ሺህ ያህል የተቀናቃኝ ጦር ተደምስሷል፡፡ ከእኛ ግን 18 ብቻ ነው የሞተው፤ ተከቦ ከነበረው፡፡
የቋንቋና የባህል ችግር አልገጠማችሁም?
እኛ ከማንም ጋር ግንኙነት የለንም፡፡ ግንኙነት ያለው ከዋናው መምሪያ ነው፡፡ አገናኝ መኮንኖች እዚያ የተባለውን ይነግሩናል እንጂ ከሕዝብ ጋር በፍፁም አንገናኝም፡፡ ስንገናኝም በጥቅሻ ነው፡፡ ያለነው እልም ያለ ገጠር ውስጥ በመሆኑ ከተማ ወጥቶ በእረፍት ጊዜ መዝናናት የሚባል ነገር የለም፡፡ ብንታመም ሻምበላችን ውስጥ ሕክምና አለ፡፡ አንድ ጊዜ ታምሜ ነበር፡፡ እዚያ ታክሜ ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ሌላ ሀኪም ቤት ተላኩ፤ ወዲያውኑ በሄሊኮፕተር ፑዛን ከተማ ሄድኩ፡፡ ለ20 ቀን ያህል ታክሜ ተመልሻለሁ፡፡ ሕክምናቸው በጣም ጥሩ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ከዚያ ሀገር ሴት ጋር በፍቅር መውደቅ ጋብቻ እና የመሳሰሉት አይኖሩም?
ጋብቻ ሳይሆን ከጋብቻ ውጪ ከዚያ ሀገር ሴቶች ልጅ የወለዱ ወታደሮቻችን አሉ፤ ከኮሪያ ሳይሆን ከጃፓን ፍቃድ ስንወጣ ጃፓን ነበር የምንሄደው፡፡ ፍቅር ይዟቸው ሲለያዩ የተላቀሱም አሉ፡፡
እርስዎስ?
እንዲህ አይነት ጣጣ ውስጥ አልገባሁም፡፡ ጃፓን ፍቃድ ሄጃለሁ፡፡ ግን ልጅነትም አለ፡፡ ሀኪም ቤት ውስጥ በተኛሁ ጊዜ ግን አንድ ችግር ገጥሞኛል፡፡
ምን አይነት ችግር?
አንዲት ነጭ አሜከካዊት ሻምበል የሕክምና ባለሙያ ነበረች፡፡ ፑዛን ጋውን ለብሳ መጣች፡፡ አልኮል የፈሰሰበት ሙቅ ውሃ እና ፎጣ ይዛ ገላህን ልጠበው ልሸው አለችኝ፡፡ በፍፁም እንዴት ተደርጐ አልኳት፡፡ በኋላ አሁን ስሙን የረሳሁት አስተርጓሚ ጠራች፡፡ ለምን እምቢ ትላለህ ገላህን ልጠብህ እኮ ነው ያለችህ አለኝ፡፡
ከዚህ ስሄድ እንኳን ላገባ ሴት አላውቅም፡፡ ራሴ መታጠብ ስችል ሴት እንዴት ያጥበኛል አልኩ፡፡ ሳቀብኝና ነግሯት ለኔ ችግር የለውም አለኝ፡፡ በኋላ ስታጥበኝ የሷንም ፍላጐት በማየቴ ሰውነቴ ጋለ፤ ፍላጐቴ ተነሳሳ፡፡ ይኼኔ “ኧረ ባክህ” ብዬ ስነግረው ሳቀና ነገራት፡፡ ችግር የለውም ብላ አንድም የሰውነቴ ክፍል ሳይቀር አገላብጣ አጠበችኝ፡፡ ትንሽ ቆይታ ልብሷን ለውጣ ለእኔም ልብስ ይዛ መጣች፡፡ ይዛኝ ሄደች፡፡ የዚያኑ እለት ግንኙነት አደረግን፡፡
የመጀመሪያዬ እሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደሆነ ጠላኋት፡፡ ተመልሼ ሀኪም ቤት ተኛሁ፡፡ ሳያት ሁሉ እሸፋፈን ነበር፤ ከጥላቻዬ የተነሳ፡፡ ሳልቆይ ለአለቃዬ ለአስተርጓሚው ነገርኩት፡፡ ድኛለሁ ይላል ይውጣ ተባለ፡፡ እሷ አይወጣም ብላ እንደገና ስምንት ቀን አቆየችኝ፡፡ ከአንዴ በላይ አብረን አልወጣንም፤ እምቢ አልኩ፡፡ በዚሁ መንስኤ ለ15 ቀን ታምሜአለሁ፡፡
ሕክምና ሳይጨርሱ ነው ከሻምበሏ ጋር የወጣችሁት?
ሕክምናማ ጨርሼ እኮ ነው መታጠቡ የመጣው፡፡
ጥሬ ስጋ ስትበሉ የውጭ ዜጐች አይተው ይሸሹዋችሁ ነበር የሚባለው እውነት ነው?
ይኼንን እኔም እንዳንተው ነው የሰማሁት፡፡ ይህንን አደረገ የተባለው ሻለቃ ተፈራ ወልደትንሣኤ ነው ይባላል፡፡ ከመጀመሪያ ዙር ዘማቾች፡፡ እንደዘመተ መንጉሱ በማቀዝቀዣ ታሽጐ ቁርጥ ሥጋ ይላካል - ለጦሩ ንጉሱ የላኩላችሁን ተመገቡ ተብሎ ምግብ ቤት (ሚንስ ቤት) ይመገባሉ፡፡ የጦሩ አባላት ተመግበው የተረፈውን የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ የምንሰጥበት እቃ አለ፡፡ ያን ሥጋ በላስቲክ ጠቅልሎ ይዟል መሠለኝ፡፡ በልቶ ሲጠግብ ጦርነት ይታዘዛል፡፡
ከውጊያ በኋላ ድል አድርገው ሲጨረሱ በድካምና በረሃብ ቁጭ ይላሉ፡፡ በያዘው ሴንጢ እየቆረጠ ያንን ሥጋ ይበላል፡፡ ይህንን አንዲት ቻይናዊት ፈርታ ተደብቃ አይታዋለች፡፡ ደንግጣ ሰው የሚበሉ እንግዳ ሰዎች መጡ ብላ አስወራች፡፡ ከዚያን ወዲህ ነው እንዲህ መወራት የጀመረው፡፡ ሰው በላ መጣ አሉን፡፡
እርስዎ በስንት የጦር ግንባሮት ተሳትፈዋል?
ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ዮክ ተራራ የጦር ግንባር ነው፡፡ ሁለተኛው ችቦ ነው፡፡ ከነዚህ ውጪ የለም፡፡
በጣም የሚያስታውሱት የኢትዮጵያም ሆነ የሌላ ሀገር ወታደር?
አንድ ግዳጅ ላይ አንድ የመቶ አዛዥ ማንደፍሮ የማነህ ይባላሉ፡፡ ቅኝት ይወጣሉ፡፡ የኛ ሰራዊት ቅኝት ከመውጣቱ በፊት አሜሪካ የማረከቻቸውን የቻይና ወታደሮች አሰልጥና በስለላ ታሰማራ ነበር፡፡ ለእነሱና ለእኛ የተሰጠው ቦታ የተለያየ ነው፡፡ ለመቶ አለቃው ተነግሯል፡፡ ቻይናዎቹ የኛን ይዞታ ይዘው ይጠብቋቸዋል፡፡
የኛዎቹ ሊይዙ ሲሉ ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ የሞቱት ሞቱ፡፡ ቁስለኞችን ውሰዱ ተባልን፡፡ በዚያን ጊዜ እኔ ተመለመልኩና ሂድ ቁስለኛ አምጣ ተብዬ ተላኩኝ፡፡ በሸክም ነው የምናመጣው፤ ያውም ተራራ እና ጨለማ ነው፡፡ ተሸክሜ ሳንጃ ሰክቻለሁ፣ ጠመንጃዬ እንደጎረሰ ነው፡፡ ተሸክሜ ዳገት እየወጣሁ ትንሽ ሲቀረን አንሸራቶኝ ስወድቅ ሰውየውም ወደቀ፡፡ እኔን አጥፍቶ ሊያመልጥ ሲያስብ ቻይናዊው ቀና ብሎ ይቃኛል፣ ቶሎ ብዬ ርምጃ ወሰድኩ፡፡
አሁን ኑሮ እንዴት ነዉ?
የቀበሌ ቤት ተከራይቼ ነው የምኖረው፡፡ እዚህ የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበር በጥበቃ ሰራተኝነት አገለግላለሁ፡፡ ፍላጎት ያለው ያገልግል ሲባል ተቀጠርኩ፡፡ ከምኖርባት ሽሮሜዳ አፍንጮ በር በእግር መንቀሳቀሱን ወድጄዋለሁ፡፡ ደመወዙ ግን አይወራም አይጠቅምም፡፡
ዘጠኝ ልጆች አሉኝ፡፡ ሦስቱ አግብተዋል፡፡ ሌሎቹ ገና ናቸው፡፡ አንደኛው ልዴ መለሰ ዘነበወርቅ ይባላል ደቡብ ኮርያ ለትምህርት ቢሄድም ከእኔ ጋር እንዳለ ነው የሚቆጠረው፡፡ 249 ብር ነበር የሚከፈለኝ በብዙ ጭቅጭቅ ለቀን እንሄዳለን ስንል ነው መሠለኝ 294 ብር ሆኗል፡፡ የጡረታ አበሉ 310 ብር ነው፡፡ በፊት ደመወዛችን 15 ብር ነበር፡፡ ያውም አምስቱ ብር ተያዥ ነው፡፡ 10 ብር እንቀበላለን፡፡ ሦስት ኪሎ ስንዴም ይሰፈርልናል፡፡ ቤተሰብና ትዳር ስለሌለን ብር ከሃምሳ ሸጠናት ከሰልና ሳሙና እንገዛበት ነበር፡፡
ትዳርስ እንዴት መሠረቱ?
በ1957 ዓ.ም በ32 ዓመቴ ነው ያገባሁት፡፡ እናት አባቴ ናቸው የዳሩኝ፡፡ ከሰራዊቱ ወጥቼ በሲቪል ስራ ላይ ነበርኩ - አየር መንገድ ውስጥ፡፡ አባቴን ከሀገር መውጣቴ ካልቀረ አልመለሥም ዳረኝ ስለው እሺ አለ፡፡ አግኝቼልሃለሁና ናና እያት አለኝ፤ ሰሜን ሸዋ ደብረሊባኖስ አካባቢ ነው የቤተሰቦቼ ቤት፤ ሄድኩ፡፡
አይንህ አይኔ፣ አንደበትህ አንደበቴ ነው፤ ማየቴ ምን ጥቅምና ትርፍ አለው፤ አንተ ባየኻት እስማማለሁ አልኩት፡፡ ያየሁአት የሰርጉ እለት ነው፡፡ የሰርጉ እለት ስገባ ሴቶቹ በሀገራችን ባህል መሠረት ተሸፋፍነዋል፡፡ እናት አባቷንም አላውቅም፡፡ ወላጅ አባቷ ማነው አልኩ? እኔ ነኝ አሉ፡፡
እርስዎ ነዎት? ስል አዎ አሉ፡፡ ያውቁኛል ስል ኧረ ልጄ አላውቅህም አሉኝ፡፡ ዘነበወርቅ በላይነህ እባላለሁ አልኳቸው፡፡ አንተ ነህ ሲሉኝ አዎ … ልጅም ፈቅደውልኛል ሲላቸው አዎ አሉኝ፡፡ በሉ ስለማላውቃት ይስጡኝ አልኳቸው፡፡
ገልጠው ይቺ ነች ልጄ አሉ፡፡ ተሞሽራ ከተቀመጠችበት፡፡ ወ/ሮ አሥራት አለሙ፣ የልጆቼን እናት፣ ባለቤቴን እንደዚህ ነው ያገባኋት፡፡ አገር ቤት ተጋባንና አዲስ አበባ ሽሮሜዳ መኖር ጀመርን፡፡