ዐቢይ አህመድ
AShebre15ኛውና የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር / From Wikipedia, the free encyclopedia
አብይ አህመድ አሊ (በኦሮምኛ፡ Abiyi Ahmed Alii ፣ በእንግሊዝኛ Abiy Ahmed Ali የተወለዱት : ነሐሴ 9 ቀን 1968 ) ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ሲሆኑ ከመጋቢት 24 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 4ኛ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ። ኢትዮጵያን ለ28 ዓመታት የገዛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 3ተኛ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆኑ በዚያ ቦታ ላይ የመጀመሪያው የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ ናቸው። አብይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሲሆኑ በ2011 ዓ.ም ኢህአዴግ ፈርሶ የብልጽግና ፓርቲ እስኪመሰርት ድረስ ከኢህአዴግ አራት ጥምር ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አባል ነበሩ። ለ20 አመታት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የነበረውን ግጭትና አለመግባባት ለማስቆም በሰሩት ስራ የኤ.አ 2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸንፈዋል።
ዐቢይ አህመድ አሊ | |
---|---|
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ2010 | |
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር | |
2010 | |
ቀዳሚ | ኃይለማሪያም ደሳለኝ |
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር | |
ከ2007ዓ.ም. እሰከ 2008ዓ.ም. | |
የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ | |
ከ2000ዓ.ም. እሰከ 2003ዓ.ም. | |
የተወለዱት | ጂማ፣ ኢትዮጵያ |
የፖለቲካ ፓርቲ | ብልፅግና |
ዜግነት | ኢትዮጵያ |
ባለቤት | ዝናሽ ታያቸው(Zinash Tayachew) |
ልጆች | 4 |
ሀይማኖት | ጴንጤቆስጤያዊ ክርስትና |
ማዕረግ | ሌተናንት ኮሎኔል |
አቶ አብይ በ2012 ዓ.ም ሰኔ ወር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ሊካሄድ የታቀደውን የፓርላማ ምርጫ ለማራዘም ወስነዋል። ይህ እርምጃ በተለይ ከተቃዋሚዎች በኩል ትችት የፈጠረ ሲሆን ህገ መንግስታዊ ሕጋዊነት ጥያቄ አስነስቷል።
በጥቅምት 2013 በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የመከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ ጦር ከህወሓት ሃይሎች ጋር ላደረጉት የትግራይ ጦርነት መነሻ ነበር[1][2][3][4][5][6]