ጥቅምት ፲፩
- ፲፯፻፺፰ ዓ.ም. - በታዋቂው የብሪታንያ የባህር ኃይል አበጋዝ ሆሬሽዮ ኔልሰን መሪነት ከፈረንሳይና ከእስፓኛ ከተውጣጣ የባሕር ኃይል ጋር የትራፋልጋር ውጊያ (Battle of Trafalgar) እየተባለ በታሪክ በሚታወቀው ጦርነት የብሪታንያ ኃይል ድልን ተቀናጀ። ሆሬሽዮ ኔልሰንም በዚሁ ውጊያ ሞተ።
- ፲፰፻፸፩ ዓ.ም - ከጨሊዛ(carbon) የተሠራ ክር በመጠቀም ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የመጀመሪያውን የጾፓስ(electric) መብራት ብልቃጥ ሞከረ። ይኼውም መብራት ከመቃጠሉ በፊት ለ ፲፫ ሰዐት ተኩል አበራ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የሮማ ኦሊምፒክ የማራቶን ድል አድራጊው አበበ ቢቂላበቶክዮ ውድድር የራሱን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰከንድ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ድልን ተቀዳጀ። ከዚህ ድል ከሰላሳ ስድስት ቀናት በፊት ትርፍ አንጀቱን በቀዶ ሕክምና አስወግዶ ስለነበረ፣ ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳያገግም በአዲስ ክብረ ወሰን ማሸነፉ በማራቶን ውድድር እስካሁን ድረስ አቻ የለሽ ጀግና አድርጎ አስመስክሮለታል።