እንዳስላሴ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሽረ እንዳሥላሴ የሽረ ምድር ትልቋ ከተማ ስትሆን ከአሁን በፊት የነበረችውን ጥንታዊት የዓዲ ወንፊቶ 1 ከተማ ወራሪው ጣልያን ኢትዮጵያ በወረረበት ወቅት ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ካወደማት በኋላ በማይማፃ በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሥር በ1930 ዓ/ም የተመሰረተች ከተማ ናት፡፡ ከተማዋ ከጥንታዊው የማይተሮኽሮዃ ማይድራሻ በቅርብ ርቀት ስትሆን የጭልሜዳ፣ወቓር ዱባ፣ጩማይ2፣ዓዲ ፍልሖ ሜዳዎች እንዲሁም የማይዑመት ጎቦ አንጠልጢላ፣እምባ መለኸዅስም ኮረብቶች እንዲሁም የለዃምባ ጊዮርጊስና የቈየፃ ገዳማት ተራራዎችም በግርማ ሞጎስ የሚጠብቋት ውብ ከተማ ናት፡፡
እንዳስላሴ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በምዕራባዊ ዞንና በታህታይ ቆራሮ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ43,967 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 21,333 ወንዶችና 22,634 ሴቶች ይገኙበታል።[1]. የከተማው አቀማመጥ በ13°52′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
ከታላቋ ሽረ እንዳሥላሴ ከተማ ሌላ ሑመራ፣ ማይፀብሪ፣ ዓዲ ገብሩ፣ እንዳባጉና፣ ሸራሮ፣ ዓዲጎሹ፣ ሰለኽለኻ፣ ሰመማ፣ ደብረ ከርበ፣ ክሳድ ጋባ፣ ባድመ፣ ዓዲ ዳዕሮ፣ ዓዲ ነብርኢድ፣ ዓዲ ሃገራይ፣ ዓዲ አውዓላ፣ ዓዲ ረመፅ፣ ቆራሪት፣ ከተማ ንጉሥ፣ ኣደባይ፣ ባዕኸር፣ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ማይ ሓንሰ፣ ጭላ የሚባሉ ከተሞች ሲኖሩ ሌሎች የቀበሌ ትናንሽ ከተሞችም በዙርያዋ አሉ፡፡