ኖቪያል
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኖቪያል (novial) በኦቶ የስፐርሰን በ1920 ዓ.ም. የተፈጠረ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ቃላቱ በተለይ ከጀርመንኛና ከሮማንስ ቋንቋዎች የተመሠረተ ነው። የስፐርሰን በ1935 ዓ.ም. ሲሞቱ ሀሣቡ በሥራ እንዳይውል ተደረገ። በ1980ዎቹ ግን ከኢንተርኔት የተነሣ አዲስ ትኩረት ተሰጥቶታል። እንደ ኤስፔራንቶ ፈጣሪ ዛምንሆፍ ሳይሆኑ የዴንማርክ ዜጋ የሆኑ አቶ የስፐርሰን ባለሙያ የቋንቋ ሊቅ ነበር። በሌሎች ሠው ሠራሽ ቋንቋዎች የተገኘው ቅጥ የሌለው ዘዴ አልወደዱም። ስለዚህ በቋንቋ ጥናት መርሆች ላይ የተመሠረተ ቋንቋ ለመፍጠር ጣሩ።