ሞላ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሞላ ማለት ተለጣጭ መሳሪያ ሲሆን የተንቀሳቃሽ አቅሞችን በማከማቸት ወደ እምቅ አቅም ይቀይራል። ሞላወች ብዙ ጊዜ ከጠነከረ አረብረት(steel) ይሰራሉ። በ#የሁክ ህግ መሰረት፣ በሞላ ላይ የሚያርፍ ጉልበትና የሞላው የርዝመት ለውጥ ተመጣጣኝ ናቸው። የዚህ ምጥጥን ውድር የሞላ ቋሚ ቁጥር በመባል ይታወቃል። ማለት የሞላው ቋሚ ቁጥር የሚሰላው በሞላው ላይ በሚያርፈው ጉልበት ሲካፈል በዚህ ጉልበት ምክንያት በመጣው የርዝመት ለውጥ ነው።
ሽክርክር የሆነ ሞላ መሰራት የጀመረው በ15ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን ነገር ግን የጥንቱ አይነት የቀስት መወርወሪያ ሞላ የተሰራው ከታሪክ በፊት በሚኖሩ ህብረተሰቦች ነው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን የእንግሊዙ ተመራማሪ ሮበርት ሁክ የሞላን የተፈጥሮ ህግጋት ለማጥናት በመቻሉ ሂሳባዊ ቀመሩን ለማስቅመጥ በቅቷል።